ያሁ (yahoo)አሜሪካ የሚገኝ የኮምፕዩተር አገልግሎቶች የሚሰጥ ድርጅት ነው። የያሁ ኢ-ሜይልያሁ ዌብሳይት ማውጫ እና ሌሎች አገልግሎቶችን ያቀርባል። ከስታንፎርድ በተመረቁት ዴቪድ ፊሎ እና ጄሪ ያንግጃንዩዌሪ 1994 እ.ኤ.አ. ነው የተመሠረተው። የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት በሰኒቬል፥ ካሊፎርኒያ ይገኛል።

ያሁ (Yahoo, Inc) www.yahoo.com
150px|
ኢንዱስትሪ ኢንተርኔት
ዓይነት የሕዝብ
የምስረታ_ቦታ ሳንታ ክላራካሊፎርኒያ (ማርች 2፣ 1995 እ.ኤ.አ.)
ዋና_መሥሪያ_ቤት ሰኒቬልካሊፎርኒያአሜሪካ
ገቢ $5.257 ቢሊዮን (2005 እ.ኤ.አ.)
የተጣራ_ገቢ $5.257 ቢሊዮን (2005 እ.ኤ.አ.)
የሰራተኞች_ብዛት 11,000 (2006 እ.ኤ.አ.)

እንደ አሌክሳ ኢንተርኔት እና ኔትክራፍት ዓይነት የኢንተርኔት አጠቃቀምን የሚመዘግቡ ድርጅቶች በኩል፣ ያሁ ከ400 ሚሊዮን በላይ የሆኑ ሰዎች የሚጎበኙት ሲሆን፣ ይህም በኢንተርኔት ከሚጎበኙ ዌብሳይቶች አንደኛ ያደርገዋል።